ያደረግነው ጥረት
ተፃፈ በገድሉ መኮንን
አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፭ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት
ጥረት ስንጀምር አስበን ለለውጥ
ውጣ ውረድ አለው ተስፋ የሚያስቆርጥ
እንደሚጨልመው ሊነጋ ሲል ሌቱ
ይበዛል ችግሩ ግራ መጋባቱ
የጠበቁት ነገር የጓጉለት ጉዳይ
ውጤቱ እስኪታወቅ አለው ብዙ ስቃይ
እልባት ግን ሲያገኝ በመጥፎ ወይ ጥሩ
እንኳን ትዝ ሊለን ስቃዩ ችግሩ
ይገርማል ስንረሳው እስከመፈጠሩ
ደስታን አይፈጥርም ያገኘነው ውጤት
ውጣ ውረዱ እንጂ ያደረግነው ጥረት